በርካታ ወንዞች ያሏቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት
በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንዞች አሉ
ሩሲያ የ100ሺህ ወንዞች ባለቤት በመሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚዋ ናት
በርካታ ወንዞች ያሏቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በአለም አቀፍ ደረጃ 3 ሚሊየን ወንዞች ሲኖሩ እነዚህ ወንዞች በአካባቢጥበቃ፣ ለተፈጥሮ ሚዛን ማስጠበቂያ፣ አልፎ ተርፎም ለሰው ልጆች እድገት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ጉዙፍ የአለም ቀደምት የሰው ልጅ ስልጣኔዎችም ወንዞችን ተከትለው የተመሰረቱ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
ቀደም ባለው ዘመን ከእርሻ እና መጠጥ አገልግሎት ባለፈ ጥቅም ላይ ያልዋሉት ወንዞች አሁን ላይ የግዙፍ ጂኦፖለቲክሳዊ ውዝግቦች ማስነሻ ፣ የሀይል እና የኢኮኖሚ ምንጭም በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡
ሩሲያ የ100 ሺህ ወንዞች ባለቤት በመሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚዋ የበርካታ ወንዞች ባለቤት ናት፡፡ የአማዞን ፣ የናይል እና የሚሲሲፒ ወንዞች በእርዝመታቸው በቀዳሚነት ከሚጠሩት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
የበርካታ ተፈጥሯዊ ሀብቶች መገኛ የሆነችው አፍሪካ 55 አህጉሪቷን አቋርጠው የሚወጡ አለም አቀፍ ወንዞች ባለቤት ናት፡፡
አህጉሪቷ ለኤሌክትሪክ ሀይል፣ ለአሳ ሀብት ልማት እና ለመስኖ ልማት ሊውሉ የሚችሉ የበርካታ ወንዞች ባለቤት ብትሆንም በተገቢው ልክ አልተጠቀመችባቸውም፡፡
ስታቲስታ በአፍሪካ በርካታ ወንዞች የሚገኙባቸው የአፍሪካ ሀገራት በሚል ባስቀመጠው ዝርዝር ማዳጋስካር ፣ አልጄሪያ እና ሞዛምቢክን በደረጃ አስቀምጧቸዋል፡፡