5 ሽህ ካቶሊካዊያን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ተጠመቀበት ዮርዳኖስ ወንዝ በመጓዝ ጥምቀትን አከበሩ
ካህናቱ የወንዙን ውሃ ባርከው ተሰብሳቢዎቹን በመርጨት በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ የክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ ተካሂዷል
በፈረንጆቹ 2022 በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አንድ ሽህ ሰዎች ብቻ በበዓሉ ተካፍለዋል
በሺዎች የሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች በዮርዳኖስ ወንዝ ምስራቃዊ ዳርቻ ወደሚገኘው "ጥምቀት" ቦታ በመሰብሰብ ዓመታዊ የጥምቀት በዓልን አክብረዋል።
በፈረንጆቹ 2022 በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት እየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀበት ወንዝ አንድ ሽህ ሰዎች ብቻ በበዓሉ ለይ ተሳትፈዋል።
ከአማን በስተ ምዕራብ 50 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው “አል-መግታስ” በሚገኘው “የክርስቶስ ጥምቀት ቤተ ክርስቲያን” በተካሄደው ቅዳሴ ላይ ከአምስት ሽህ በላይ ሰዎች ተገኝተዋል።
በፈረንጆቹ 2021 የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ጥብቅ የጤና እርምጃዎች በመውሰድ ምዕመናን በሌሉበት በቀሳውስት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ተካሂዷል።
በዮርዳኖስ የሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቃል አቀባይ አባ ሪፋት በድር ባደረጉት ንግግር “በእርግጥ የኮሮና ወረርሽኝ ካበቃ በኋላ ይህ የመጀመሪያው ጉዞ ነው፤ ባለፈው ዓመት በአንድ ሽህ ሰዎች ብቻ ተከብሯል” ብለዋል።
አክለውም "ይህ መልካም ጉዞ 23ተኛው ነው። ወደዚች ቅድስት ስፍራ የሚደረገው ጉዞ ከአምስት ሽህ በላይ የሚሆኑ ከከተማችን፣ ከመንደሮቻችን እና ከካቶሊክ ቤተክርስቲያናችን የተውጣጡ ምዕመናንን ተቀብለናል" ብለዋል።
በኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ መሪነት በደርዘን የሚቆጠሩ ካህናት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በዜማ ታጅበው ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመግባታቸው በፊት የውሃውን ጋኖች ሞልተዋል ነው የተባለው።
ካህናቱ የወንዙን ውሃ ባርከው ተሰብሳቢዎቹን በመርጨት በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ የክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ ተካሂዷል።
ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ በሚገኘው በቢታንያ መንደር በዋዲ አል-ካራር የሚገኘው “ጥምቀት” ቦታ እና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስ ላይ በፈረንጆቹ 2015 ተካቷል።