ክሱ በፈረንጆቹ 2014 ቢጀመርም፤ሊባኖስ በሀሪሪ ግድያ ላይ ፍትህ ለማግኘት 15 አመታት ፈጅቶባታል
ክሱ በፈረንጆቹ 2014 ቢጀመርም፤ሊባኖስ በሀሪሪ ግድያ ላይ ፍትህ ለማግኘት 15 አመታት ፈጅቶባታል
በፈረንጀቹ 2005 በተፈጸመው የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ራፊቅ ሀሪሪ ግድያ ቀዳሚ ተከሳሽ የነበረው ግለሰብ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ተብሏል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚታገዘው ሊባኖስ ችሎት ሳሊም አያሽ የሂዝቦላ ቡድን ታጣቂ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ተገኝቶበታል በማለት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
ከሳሊም አያሽ ጋር አብረው ተከሰው የነበሩት ሀሰን ሀቢብ መርሂ፣ሁሴን ሀሰን ዋነሲና አሳድ ሀሰን ሳብራ በነጻ ተለቀዋል፡፡ ፍርዱ በዴቪድ ሪ በተባሉት ዳኛ ሲነበብ፤ ፍድርቤቱ ሶስቱ ተጠርጣሪዎች በበቂ ሁኔታ በፍንዳታው ጋር እንደማይገናኙ በመጥቀስ የምርመራውን ምሰሶ አሳውቋል፡፡
ዳኛው እንዳሉት በሶስት ተከሳሾች ላይ ከጥርጣሬ ያለፈ በሀሪሪ ግድያ መሳተፋቸውን ማረጋገጥ አይቻልም ብሏል፡
ችሎቱን የመሩት ዳኛ ፍርዱን ሲያነቡ ምንምእንኳን አያሽ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ግንኙነት እንዳለው ቢታወቅም፣ የታጣቂው ሂዝቦላ ቡድንና የሶሪያ መንግስት በፈረንጆቹ 2005 በተፈጸመው ግድያ ላይ ስለመሳተፋቸው የሚያሳይ መረጃ የለም ብለዋል፡፡
ችሎቱ ሶሪያና ሂዝቦላ ሀሪሪንና የሱን የፖለቲካ መሪዎች ለማጥፋት ፋላጎት እንዳላቸው ዳኛ ዴቪድ ሪ ተናግረዋል፡፡
ነገርግን ዳኛው እንዳሉት የሂዝቦላ አመራር በግድያው ስለመሳተፉና የሶሪያ መንግስትም ስለመሳተፉ የሚያሳይ መረጃ የለም ብለዋል፡፡ የፍርዱ ሂደት የተጀመረው ማክሰኞ እለት በኔዘርላንድ ነው፡፡
ክሱ በፈረንጆቹ 2014 ቢጀመርም፤ሊባኖስ በሀሪሪ ግድያ ላይ ፍትህ ለማግኘት 15 አመታት ጠብቃለች፡፡ በሄግ አቅራቢያ በሚገኘው ሊድሼንድማን የተሰየመው ችሎት 297 ምስክሮችን የሰማ ሲሆን 415 ቀናትም ፈድቷል፡፡ በችሎቱ የራፊቅ ሀሪሪን ልጅ ጨምሮ በርካታ ቤተሰቦች በችሎቱ ተገኝተዋል፡፡