የግል ንግድ ባንኮች 1 ዶላርን እስከ 113 ብር እየገዙ፤ እስከ 127 ብር እየሸጡ ይገኛሉ
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጠቅምት 1 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ተመን አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ112.3957 ብር እየገዛ በ123.6353 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክም በመደበኛው የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112.9888 ብር እየገዛ በ127.1124 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የገለጸው።
ንብ ባንክም መደበኛውን (እለታዊ የምንዛሬ ተመን) ይፋ አድርጓል።በዚህም ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113.0428 ብር እየገዛ በ126.6079 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።