የመስከረም 29 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?
የግል ንግድ ባንኮች 1 ዶላርን እስከ 113 ብር እየገዙ፤ እስከ 127 ብር እየሸጡ ይገኛሉ
ባንኮች ከውጭ በሃዋላ ለሚላክ ዶላር ያቀረቡት ልዩ የበዓል ተመን ነገ ይጠናቀቃል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ መስከረም 29 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ተመን አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ112.3957 ብር እየገዛ በ123.6353 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የምንዛሬ ዋጋ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም በሃዋላ የሚላክ 1 ዶላርን ከመደበኛው የምንዛሬ ዋጋ ላይ እስከ 16 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወቃል።
ባንኩ በመደበኛው የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112.9888 ብር እየገዛ በ127.1124 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የገለጸው።
ኦሮሚያ ባንክም የአዲስ አመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከውጪ በሃዋላ የተላከ አንድ የአሜሪካ ዶላርን ከእለታዊ ተመን በተጨማሪ 17 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ እና በዚህም 1 ዶላርን በ126+ ብር እንደሚመነዝር ማስታወቁ ይታወሳል።
ባንኩ እለታዊ መደበኛ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ 1 የአሜሪካ ዶላር በ112.6310 ብር እየገዛ በ127.6529 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የጠቆመው።
እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ የሚላክን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ125 ብር እንደሚመነዝር ያስታወቀው ንብ ባንክም መደበኛውን (እለታዊ የምንዛሬ ተመን) ይፋ አድርጓል።
በዚህም ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113.0428 ብር እየገዛ በ126.6079 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።