ኢኮኖሚ
በመስከረም 30 2017 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ስንት ብር ገባ?
የግል ንግድ ባንኮች 1 ዶላርን እስከ 113 ብር እየገዙ፤ እስከ 127 ብር እየሸጡ ይገኛሉ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላር በ112 ብር እየገዛ፤ በ123 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ መስከረም 30 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ተመን አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ112.3957 ብር እየገዛ በ123.6353 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክ በመደበኛው የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112.9888 ብር እየገዛ በ127.1124 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የገለጸው።
ንብ ባንክም መደበኛውን (እለታዊ የምንዛሬ ተመን) ይፋ አድርጓል። በዚህም ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113.0428 ብር እየገዛ በ126.6079 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ በንክም በእለታዊ መደበኛ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ 1 የአሜሪካ ዶላር በ112.6310 ብር እየገዛ በ127.6529 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የጠቆመው።