የጥቅምት18 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን የመግዣ ዋጋ 116 ብር ያደረሰ ሲሆን፤ መሸጫውንም ወደ 119 ብር ከፍ አድርጓል
የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ119 እስከ 121 ብር መግዣ፤ ከ119 እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 18 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ባሳለፍነው ሳምንት የነበረውን አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ116.6699 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ119.0033 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ዛሬም ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ የጥቅምት 18 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አንበሳ ባንክም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ ካቀረቡት ውስጥ ሲሆን፤ ባንኩ የጥቅምት 18 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ120.6235 ብር እየገዛ በ123.0360 ብር እየሸጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.3995 ብር ገዝቶ በ121.7875 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው ያስታወቀው።
ዳሽን ባንክም የጥቅምት 18 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ119.2255 ብር እየገዛ መሆኑን ገልጿል። 121.6100 ብር የባንኩ የዶላር መሸጫ ዋጋ ነው።