በጥቅምት 16 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር ስንት ብር ገባ?
የግል ንግድ ባንኮች 1 ዶላር ከ117 እስከ 121 ብር ገዝተው፤ ከ119 እስከ 123 ብር እየሸጡ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትናንቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስትም ባንኮች የሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 16 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ116.6699 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ119.0033 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ የጥቅምት 16 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑ ላይ ማሻሻያ ባያደርግም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ጎህ ቤቶች ባንክ ከኦሮሚያ ባንክ በመቀጠል ከፍተኛ የዶላር መግዣ ዋጋ ያቀረበ ባንክ ነው። ባንኩ አንድ ዶላር በ121.0353 ብር ገዝቶ በ123.4560 ብር እየሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
ጸደይ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 16 2017 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን የምንዛሬ ተመን ይፋ ሲያደርግ ለ1 ዶላር 120.1170 ብር መግዣ፤ 122.5193 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥቷል።
ዳሽን ባንክ የትናንቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2255 ብር እየገዛ ፤ በ121.6100 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አቢሲኒያ ባንክ ደግሞ አንድ ዶላር በ119.2258 ብር ገዝቶ በ121.6103 ብር እየሸጠ መሆኑን በእለታዊ ተመኑ አመላክቷል።