የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ117 እስከ 121 ብር መግዣ፤ ከ119 እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 15 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ116.6699 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ119.0033 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ዛሬም ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ የጥቅምት 15 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣው ላይ ከትናንቱ ከ4 ብር በላይ ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.3905 ብር ገዝቶ በ121.7783 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው ያስታወቀው።
ዳሽን ባንክ ከትናንቱ ተመን የሳንቲሞች ማሻሻያ አድርጎ አንድ ዶላርን በ119.22255 ብር እየገዛ መሆኑን ገልጿል። 121.6100 ብር የባንኩ የዶላር መሸጫ ዋጋ ነው።