ምርጫ ቦርድ የካቲት 22 ሊጀመር የነበረውን የመራጮች ምዝገባ ወደ መጋቢት 16 አራዘመ
የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 16 እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል
ምርጫ ቦርድ ቀኑን ያራዘመው የእጩ የአስፋጻሚዎችን ገለልተኝነት ለማጣራት ጭምር መሆኑን አስታውቋል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ እንዲጀመር ቀደም ብሎ ካስቀመጠው የካቲት 22 ፣2013 ወደ መጋቢት 16፣2013 ማራዘሙን አስታውቋል፡፡
ቡርዱ ቀኑን ያራዘመው “… ከክልሎች የሚገኘው የቢሮዎች ትብብር በመዘግየቱ፣ የእጩዎች ምዝገባ ቀናት ከተጀመሩም በኋላ ዝግጁ ያልሆኑ የተወሰኑ ቢሮዎች የነበሩ በመሆኑና ፓለቲካ ፓርቲዎችም ተጨማሪ ቀናት በመጠየቃቸው እና የእጩዎች ምዝገባ በመራዘሙ” መሆኑን ገልጿል፡፡
ቦርዱ ከዚህ በተጨማሪም “በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ያጋጠመው የቁሳቁስ ማጓጓዝ ተግዳሮቶች በመገምገም እና የእጩ አስፈጻሚዎችን ገለልተኝነት የማጣራት ስራን በተሻለ ጥራት ለማከናወን” በማስፈለጉ ምዝገባው ምዝገባው መራዘሙን አስታውቋል፡፡
የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 16- ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ እንደሚከውን አስታውቋል፡፡
ምርጫ ቦርድ እጩዎችን የግምገማ ሂደት መገምገሙንና ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልግ መረዳቱንና የመጀመሪያ ዙር የእጩዎች ምዝገባ በተጀመረባቸው ክልሎች በአራት ቀናት ማራዘሙብ አስታቋል፡፡
“140 ሺህ በላይ እጩ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚነት የሚሰሩ ግለሰቦችን አዘጋጅቶ ገለልተኝነት ማጣራትን እያከናወነ ሲሆን፣ ይህም ከተጠበቀው ጊዜ በላይ ሊወስድ” መቻሉን ቦርዱ አስታውቋል፡፡ ምርጫ 2013 በመጭው ግንቦት 28 አንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡