እሁድ አመሻሽ ሊቨርፑል ከቼልሲ የሚደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀምራል፡፡
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 2023/24 እግር ኳስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት የሚጀመር ሲሆን የአምናው ሻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ ከአዲስ አዳጊው በርንሌይ ጋር ይጫወታሉ፡፡
የቀድሞው የማንችስተር ሲቲ አምበል እና የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ቪንሰንት ኮምፓኒ የሚሰለጥኑት በርንሌዎች በሜዳቸው ሲቲን ይገጥማሉ፡፡
ምሽት አራት ሰዓት ላይ የሚደረገው ይህ ጨዋታ አጓጊ የሆነ ሲሆን የሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ እና ከነገ በስቲያም ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡
በነገው ዕለትም ባለፈው የውድድር ዓመት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ በማንችስተር ሲቲ የተነጠቀው አርሰናል ኖቲንግሃም ፎረስትን ምሽት ላይ ይገጥማል፡፡
እንዲሁም ኒውካስትል ዩናይትድ ከአስተን ቪላ የሚያደርጉት ጨዋታ ሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ ሲሆን እሁድ ደግሞ ቸልሲ ከሊቨርፑል ይጫወታሉ፡፡
አሰልጣኝ ፖቼቲኖን የቀጠረው ቸልሲ በክረምቱ ዝውውር አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ የቀላቀለው ሊቨርፑለን ይገጥማሉ፡፡
ለዋንጫ የሚጠበቁት እነዚህ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በድል ለመጀመር አጓጊ ጨዋታ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
የፊታችን ሰኞ ደግሞ ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ዎልቭስን የሚገጥም ሲሆን ዩናይትድ ጨዋታውን እንደሚያሸንፍ ይጠበቃል፡፡
የእንግሊዝ ክለቦች ተጫዋቾችን ለማስፈረም ፉክክር ላይ ሲሆኑ የብራይተኑ ካይሴዶ በ111 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
አርሰናል አሁንም ግብ ጠባቂ እና ሌሎች ተጨማሪ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በሂደት ላይ ሲሆን ቶትንሀም፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቸልሲ አሁንም ከተለያዩ ክለቦች ጋር ድርድር ላይ ናቸው፡፡