ለሽያጭ የቀረበው የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር መሆኑን ኩባያው አስታውቋል
የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ በይፋ አስጀምሯል።
የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ ከዛሬ ጀምሮ በቴሌብር መተግበሪያ መግዛት እንደሚቻል የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ አስታውቀዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም የሀብት መጠን 100 ቢሊየን ብር መሆኑ አስታውቀዋል።
ከዚህ ውስጥ ለሽያጭ የቀረበው 10 በመቶ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፣ ይህ በብር ሲተመንም 100ሚሊየን ብር ነው ብለዋል።
ለሽያጭ የቀረበው የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር መሆኑን ያድታወቁት ስራ አስፈጻሚዋ፣ ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው ሼር 33 ሼር መሆኑን እና በብር ሲተመን 9 ሺህ 900 ብር እንደሆነም ገልጸዋል።