ተቋሙ የደንበኞቹ ብዛት ከ78 ሚሊዮን በላይ እንደደረሰም አስታውቋል
ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።
ከተገኘው ገቢ 39.9 በመቶ የድምጽ ፣ 21.7 የኢንተርኔት ፣10.2 የዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ፣ 2.5 ከቴሌብር እና 1.5 ከኢንፍራስትራክቸር እንዲሁም 5 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከዲቫይስ የተገኘ ገቢ መሆነም ተገልጿል ።
በበጀት ዓመቱ የኩባንያው የደንበኞች ቁጥር 78 ነጥብ 3 ሚሊየን መድረሱን ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ 21 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ኩባንያው በውጭ ምንዛሬ ገቢ ከሚያገኝባቸው ምንጮች 198 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለውም በ2016 በጀት ዓመት ኢትዮ ቴሌኮም 30 ቢሊዮን ብር ለመንግስት ግብር መክፈሉንም ተናግረዋል፡፡