ኢትዮ ቴሌኮም ለሽያጭ ያቀረበው የአክስዮን ብዛት ምን ያህል ነው፤ ከስንት ብር ጀምሮ መግዛት ይቻላል?
ኢትዮ ቴሌኮም የ10 በመቶ ድርሻውን ሽያጭ በይፋ አስጀምሯል
የኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ ሀብት 100 ቢሊየን ብር መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል
የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ በይፋ አስጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የድርሻ ሽያጩ በይፋ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያውያን ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን በመግዛት የኢትዮ ቴሌኮም ባለድርሻ እንዲሆኑ ጋብዘዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ ከዛሬ ጀምሮ በቴሌብር መተግበሪያ መግዛት እንደሚቻል የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ አስታውቀዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም የሀብት መጠን 100 ቢሊየን ብር መሆኑ ጠቅሰው ከዚህ ውስጥ ለሽያጭ የቀረበው 10 በመቶ ነው ብለዋል።
ለሽያጭ የቀረበው የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር መሆኑን ያስታወቁት ስራ አስፈጻሚዋ፣ ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው ሼር 33 መሆኑን እና በብር ሲተመን 9 ሺህ 900 ብር እንደሆነም ገልጸዋል።
ኢትዮ-ቴሌኮም ለሽያጭ ያቀረበው አጠቃላይ አክሲዮን ብዛት 100 ሚሊዮን መሆኑ ተገልጿል።
ከፍተኛ መግዛት የሚቻለው ሼር 3 ሺህ 333 ነው ያሉት ስራ አስፈጻሚዋ፣ በብር ሲተመን 999 ሺህ 900 ብር እንደሆነም አስታውቀዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች መግዛት እንደሚችሉ ያስታወቁት ወ/ት ፍሬህይወት፣ ተቋማት አክሲዮንን መግዛት አይችሉም ብለዋል።
የአክሲዮን ሽያጩ ዛሬ ጥቅምት ፣ 2017 እንደሚጀምር እና ታህሳስ 25፣ 2017 እንደሚጠናቀቅም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አስታውቀዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ለሽያጭ ያወጣው የአክሲዮን መጠን ቀድሞ ከሞላ ቀኑ ሳይድርስ ሊያቆም ይችላል ብለዋል።