ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ የዘጠኝ ወራት የወጪ ንግድ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አሳየ
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ከውጪ ንግድ አግኝታለች
ከተገኘው የወጪ ንግድ ውስጥ ግብርና የ77 በመቶ ድርሻ አለው ተብሏል
የኢትዮጵያ የዘጠኝ ወራት የወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አሳየ።
የንግድ እና ቀጠናዊ ውህደት ሚንስቴር እንደገለጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር።
ይሁንና የተገኘው ገቢ ግን በ1 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ተብሏል።
ለገቢው መቀነስ የጸጥታ ችግሮች፣ ህገወጥ ንግድ፣ የዓለም ንግድ መቀዛቀዝ እና የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።