የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላር በ104 ብር እገዛ፤ በ116 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 20 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 20 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ሰሞኑን ሲገዛበት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ሲሆነ ዋጋ በ104.6038 ብር እየገዛ ይገኛል። መግዣው ላይም በተመሳሳይ ጭማሪ ሳያደርግ 116.0579 ብር እየገዛ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ130.5842 ብር እየገዛ በ145.5639 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.9086 ብር እየተገዛ በ117.4976 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ110.0220 ብር እየተገዛ በ116.5000 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.7820 ብር እየተገዛ በ118.4037ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አስታውቋል።
ዳሸን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.2016 ብር እየተገዛ በ117.2268 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አስታውቋል።