የግል ንግድ ባንኮች የ1 ዶላርን እስከ 104 ብር እየገዙ እስከ 118 ብር እየሸጡ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 16 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 16 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ትናንት ሲገዛበት ከነበረው ላይ መጠነኛ ጨረማሪ በማድረግ በ104.6038 ብር እየገዛ ይገኛል። መግዣው ላይም በተመሳሳይ ጭማሪ በማደረግ 116.0579 ብር እየገዛ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ130.5842 ብር እየገዛ በ145.5639 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.9086 ብር እየተገዛ በ117.4976ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ኦሮሚያ ባንክ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.7820 ብር እየተገዛ በ116.4798 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አስታውቋል።
ዳሸን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.2016 ብር እየተገዛ በ116.4798 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።