በ2016 ከ160 ሺህ በላይ ተማሪዎች በሬሚዲያል ፕሮግራም ወደ ዩንቨርስቲዎች ይገባሉ
ተማሪዎቹ በመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚገቡ ተገልጿል
ስድስት የመንግስት ዩንቨርስቲዎች በሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል
በ2016 ከ160 ሺህ በላይ ተማሪዎች በሬሚዲያል ፕሮግራም ወደ ዩንቨርስቲዎች ይገባሉ።
ትምህርት ሚንስቴር ከአንድ ወር በፊት የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
እንደ ሚንስቴሩ መረጃ ከሆነ በዘንድሮው ዓመት በሬሚዲያል ፕሮግራም 164 ሺህ 242 ተማሪዎች ወደ መንግሥት እና ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይገባሉ።
አዲስ አበባ እና አዳማ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲዎችን ጨምሮ ስድስት የመንግስት ዩንቨርስቲዎች በዘንድሮው ዓመት የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል።
በ2015 ዓመት 145 ሺህ ተማሪዎች የሬሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ሆነዋል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 90 ሺህ ያህሉ ወደ አንደኛ ዓመት የዩንቨርስቲ ትምህርት የሚያስገባቸውን ማለፊያ ውጤት አምጥተዋል ተብሏል።