የከተራ በዓል ተከበረ
ምዕመናን መንፈሳዊ ዝማሬ በማሰማት ነው ታቦታትን አጅበው ወደ ማደሪያቸው ሸኝተዋል
በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ምዕመናን ታቦትን ከየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው በማጀብ ወደ ጥምቀተ ባህር ቦታ አድርሰዋል
በየአመቱ ጥር 10 በጥምቀት ዋዜማ የሚውለው የከተራ በዓል በኢትዮጵያ ተከብሯል።
የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ዋዜማ የሚከበረው የከተራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ እንደወትሮው ሁሉ ተከብሯል፡፡
በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ምዕመናን ታቦታትን ከየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው በማጀብ ወደ ጥምቀተ ባህር ወይም ጥምቀት ወደሚከበርበት ቦታ አድርሰዋል።
ምዕመናን በእልልታ እና መንፈሳዊ ዝማሬ በማሰማት ነው ታቦታትን የሸኙት።
የከተማዋ ዋናዋና መንገዶች በቤተክርስቲያኗ አርማ ደምቀው ይታያሉ።
በጥምቀተ ባህር ድንኳኖች ተተክለዋል፣ በተለይም በርካታ ታቦታት በሚሰባሰቡበት በጃን ሜዳ በርካታ ድንኳኖች ተተክለዋል።