የከተራ በዓል ተከበረ
ምዕመናን በእልልታ እና መንፈሳዊ ዝማሬ በማሰማት ነው ታቦታትን የሸኙት
በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ምዕመናን ታቦትን ከየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው በማጀብ ወደ ጥምቀተ ባህር ቦታ አድርሰዋል
የከተራ በዓል ተከበረ
በየአመቱ ጥር 10 በጥምቀት ዋዜማ የሚውለው የከተራ በዓል በኢትዮጵያ ተከብሯል።
በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ምዕመናን ታቦታትን ከየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው በማጀብ ወደ ጥምቀተ ባህር ወይም ጥምቀት ወደሚከበርበት ቦታ አድርሰዋል።
ምዕመናን በእልልታ እና መንፈሳዊ ዝማሬ በማሰማት ነው ታቦታትን የሸኙት።
የከተማዋ ዋናዋና መንገዶች በቤተክርስቲያኗ አርማ ደምቀው ይታያሉ።
በጥምቀተ ባህር ድንኳኖች ተተክለዋል፣ በተለይም በርካታ ታቦታት በሚሰባሰቡበት በጃን ሜዳ በርካታ ድንኳኖች ተተክለዋል።
ፎቶ/ ኢቢሲ