ኢትዮጵያዊው ብርሀኑ ለገሰ የቶኪዮ ማራቶንን አሸነፈ
ኢትዮጵያዊው ብርሀኑ ለገሰ የቶኪዮ ማራቶንን አሸነፈ
ዛሬ የተካሄደውን የቶኪዮ ማራቶን አትሌት ብርሀኑ ለገሰ 2 ሰዓት ከ 4 ደቂቃ ከ 15 ሰከንድ በመጨረስ በአንደኝነት አሸንፏል፡፡ አትሌቱ ውድድሩን ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ ነው ያሸነፈው፡፡
አትሌት ብርሀኑ ከተከታዩ አትሌት ከ30 ሰከንድ በላይ ቀድሞ በመግባት ቢያሸንፍም በ2017 ዊልሰን ኪፕሳጌ በ 2:03.58 ሰዓት የያዘውን ሪከርድ መስበር አልቻለም፡፡
ከኮሮና ስጋት ጋር በተያያዘ እንደወትሮው 30,000 የሚሆኑ የሀገሬው ተሳታፊዎች ያልተሳተፉበት ውድድሩ በመቶዎች በሚቆጠሩ አትሌቶች መካከል ነው የተካሔደው፡፡
ጃፓን 904 የቫይረሱ ታማሚዎች ይገኙባታል፤ ከነዚህም ከ700 በላይ የሚሆኑት በዳያመንድ ፕሪንሰስ ክሩይዝ መርከብ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ናቸው፡፡ ባጠቃላይ 11 ሰዎች በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል፡፡
ትውልደ ሶማሊያዊው የቤልጂየም አትሌት በሽር አብዲ ኢትዮጵያዊውን ሲሳይ ለማን አስከትሎ 2ኛ ወጥቷል፡፡
አትሌት በሽር 2:04.49 በሆነ ሰዓት ውድድሩን ሲጨርስ አትሌት ሲሳይ ለማ ደግሞ በ2:04.51አጠናቋል፡፡
ምንጭ፡- ሲጂቲኤን