ልዩልዩ
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየርመድ የሆነ ቢ777 አውሮፕላን በቻይና የእሳት አደጋ ደረሰበት
አየርመንገዱ ሁሉም አብራሪዎችና ሰራተኞች ጉዳት እንዳልደረሰባቸው አስታውቋል
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሆነ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በቻይና የእሳት አደጋ ደረሰበት
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሆነ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በቻይና የእሳት አደጋ ደረሰበት
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቢ777 እቃ ጫኝ አውሮፕላን በቻይና ፑዶንግ ሻንጋይ አየርመንገድ እቃ እየጫነ ባለበት ወቅት የእሳት አደጋ እንደደረሰበት የኢትዮጰያ አየርመንገድ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የአውሮፕላኑ የምዝገባ ቁጥር ኢቲ ኤአርኤች መሆኑን አየር መንገዱ ጠቅሷል፡፡ ጉዳት የደረሰበት አውሮፕላን እቃ መደበኛ በሆነ ፕሮግራም ከሻንጋይ ወደ ሳኦፖሎ ሳንቲያጎ የሚያመላልስ መሆኑን የጠቀሰው አየርመንገዱ ሁሉም አብራሪዎችና ሰራተኞች ጉዳት እንዳልደረሰባቸው አስታውቋል፡፡
አየርመንገዱ እሳቱን ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር መተባበሩንም ገልጿል፡፡
የእሳት አደጋው መንሰኤ በሚመለከታቸው አካላት እየተመረመረ እንደሚገኝ አየርመንገዱ አስታውቋል፡፡