በአሶሳ ተወልዶ ያደገው ሳላሀዲን ለበርካታ የውጪ እና የሀገር ውስጥ ክለቦች መጫወት ችሏል
ሳላሀዲን ሰኢድ ጫማውን ሰቀለ።
በተለያዩ ክለቦች እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለበርካታ አመታት በመጫወት የሚታወቀው ገልግሎት ሳላዲን ሰዒድ ጫማውን ሰቅሏል፡፡
ላለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ አይረሴ ታሪኮችን ያስመዘገበው ሳላዲን እግር ኳስ መጫወቱን እንዳቆመ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፈ ለሙገር ሲሚንቶ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለሲዳማ ቡና እንዲሁም ከውጪ ደግሞ ለግብጾቹ ዋዲዳግላ እና አልአህሊ፣ ለአልጀሪያው መውሊዲያ አሊደር እግር ኳስ ክለቦች መጫወት ችሏል።
በ37 ዓመቱ ራሱን ከእግር ኳስ ጨዋታ ያገለለው ሳላዲን በተያዘው ዓመት ለሲዳማ ቡና ተጫውቶ አሳልፏል።
ከብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች መካከል ተወዳጅ የነበረው ሳላሀዲን ሰኢድ ከግብጽ መልስ የልጅነት ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቢቀላቀልም በቡድኑ ውጤት ማጣት ምክንያት ወደ ሲዳማ ቡና መዘዋወር ችሏል።
ሳላሀዲን ሰዒድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ከ31 ዓመታት በኋላ በተሳተፈው ብሔራዊ ቡድን አባልም ነበር።