ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ድሆችን በማሰብና ያለውን በማካፈል ሊያከብር ይገባል- ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ
1 ሺህ 442ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ ስታድየም ተከብሯል
የእስልምና ዕመነት ተከታዮች ለታላቁ ህዳሴ ግድብ እያደረጉት ላለው ትግል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመሰገነ
1 ሺህ 442ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በዛሬው እለት በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በመከበር ላይ ይገኛል።
በዓሉ በአዲስ አበባ ከተማም የአዲስ አበባ አስልምና እምነት ተከታዮች፤የከተማ አስተዳድሩ አመራሮች እና የሀይማኖት መሪዎች በተገኙበት በተለያ ሀይማታው ስነ ስርዓቶች ተከብሯል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ባስተላፉት መልእክት፤ “የዛሬ ስራችን ቤታችን ያፈራውን እርድ ጨምሮ ሌሎችን ለተቸገሩ ወገኖች ማካፈል ነው” ብለዋል።
በዓሉ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ከጎረቤት እና ከአካባቢያችን ማህበረሰብ ጋር በፍቅር የምናሳልፈው በዓል በመሆኑ ሙስሊሞችም ይሄንን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ፕሬዘዳንቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ሃላፊ አቶ ጥራቱ በየነም ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ባለፈው የኢድ በዓል ላይ “ግድቡ የኔ ነው” በሚል ባነሮችን እና የተለያዩ ሌሎች ስለ ህዳሴው ግድብ መልዕክቶችን የሚያስተጋቡ ሀሳቦችን በማስተጋባት ግድቡ የኢትዮጵያዊያን መሆኑን ለዓለም በማድረሳችሁ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።
''ለህዳሴ ግድብ ድምጽ በመሆን እና ድጋፍ ስላደረጋችሁ በከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቀርባለሁ'' ሲሉ አቶ ጥራቱ በበዓሉ ላይ ባሰሙት ንግግራቸው ላይ ጠቁመዋል።