ምክር ቤቱ ከሳዑዲ ጎን ይቆማልም ብለዋል
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር የሳዑዲን ውሳኔ አወደሱ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር እድሪስ ሳዑዲ አረቢያ የዘንድሮው የሃጅ ስነ ስርዓት በተወሰኑ ነዋሪዎች ብቻ ይካሄዳል ማለቷን አወድሰዋል፡፡
ለውሳኔው የሳዑዲ ባለስልጣናትንም አመስግነዋል፡፡
ስነ ስርዓቱ የጥንቃቄ መርሆዎችን በመከተል ይካሄዳል መባሉ የምዕመናኑን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚያስችልም ነው ሃጅ ዑመር የተናሩት፡፡
የሪያድ የሃጅ እና ዑምራ ባለስልጣናት የዘንድሮው ሃጅ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በሃገሪቱ በሚኖሩ ጥቂት የሃይማኖቱ ተከታዮች ብቻ እንደሚካሄድ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
ሃጅ ዑመር ምክር ቤቱ ከሳዑዲ ጎን እንደሚቆም ስለማስታወቃቸውም ሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡