1495ኛው የነብዩ መሃመድ የልደት በአዲስ አበባ አኑዋር መስጅድ ተከብሯል
1495ኛው የነብዩ መሃመድ የልደት በአዲስ አበባ አኑዋር መስጅድ ተከብሯል
1495ኛው የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በመላ ኢትዮጵያ የተከበረ ሲሆን በአዲስ አበባም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ አመራሮች እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በታላቁ አንዋር መስጊድ ተከብራል፡፡
በአንዋር መጂጊድ በዓሉ ሲከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ “የሰው ልጅ የደስታ ቀኑን በተለያዩ መልኩ ያከብራል፤ እኛም ዛሬ ነብዩ መሃመድ የተወለዱበትን የደስታ ቀን ነው የምናከብረው”ብለዋል። ነብዩ መሃመድ በምድር ቆይታቸው ለረጅም ጊዜ በጦርነት ውስጥ የነበሩ ሁሉ ጦርነቱን እንዲያቆሙ ስለማድረጋቸውም አንስተዋል፡፡
ነብዩ መሃመድ አንድነትን እንድናጠናክር መክረዋል ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ ሰላምን የሰበኩ እና ሁሉም እኩል እንዲሆን ማድረጋቸውንም ገልቷል፡፡
በመሆኑም የዕምነቱ ተከታዮችም ይህንን የነብዩ መሃመድን ተግባር ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤበ አንዋር መስጊድ በነበረው የመውሊድ በዓል አከባበር ላይ አዲስ አበባ የኃይማኖት መቻቻል፣ የአብሮነት እና የአንድነት ከተማ እንድትሆን ህዝበ ሙስሊሙ ለሰራው በጎ ሥራ ምስጋና አቅርበዋል፡፡