የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ የጠፈር በር-ETRSS-1 ሳተላይት ጥቅም ምንድነው?
በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ETRSS-1 አነስተኛ የመሬት ምልከታ ሳተላይት (Small Remote Sensing Satellite) ዛሬ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ማለዳ ወደ ህዋ መጥቃለች፡፡
በቻይና መንግስት ድጋፍ በኢትዮጵያውያን የምህንድስና ጠበብቶች የተሰራችው ይህች ሳተላይት ከቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ጠፈር ምርምር ማዕከል ነው ወደ ህዋ የመጠቀችው፡፡
ከ ETRSS-1 የሚገኙ መረጃዎችንን ተንትነው የሚያነቡና የሚያቀርቡ 20 መሃንዲሶችም በቻይና ሰልጥነው ዝግጁ ሆነዋል፡፡
የመሬት ምልከታ መሳሪያዎች ሙቀትን ወይም ብርሀንን በመጠቀም ስለመሬት ሁኔታ (አቀማመጥ፣ቀለም፣ቅርጽ፣መጠን) ፣ ስለ ዕጸዋትና እንስሳት (የብርቅየ እንስሳት እንቅስቃሴ)፣ ስለ አየር ንብረት ሁኔታ፣ ስለዉሃማ አካላትና መሰል ጉዳዮች መረጃዎችን ያቀብላሉ፡፡