80 ሺህ ዶላር የሚያሸልመው የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አሸናፊነት ተጠናቀቀ
በሁለቱም ጾታ የተወዳደሩ ኢትዮጵያዊያን ከ1ኛ እስከ 12ኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረዋል
ትግስት ከተማ እና አዲሱ ጎበና የዱባይ ማራቶንን አሸንፈዋል
80 ሺህ ዶላር የሚያሸልመው የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬቷ ዱባይ የአዲሱ 2024 ዓመት የመጀመሪያውን የማራቶን ውድድር ዛሬ ማለዳ አስተናግደላች፡፡
በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ዕለት የተካሄደው ይህን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ያሸነፉ ሲሆን ውድድሩን በአንደኝነት ያጠናቀቁት አትሌቶች እያንዳንዳቸው 80 ሺህ ዶላር ተሸልመዋል፡፡
በሴቶች የማራቶን ውድድር ትግስት ከተማ አንደኛ፣ ሩቲ አጋ እና ደራ ዲዳ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመውጣት ማሸነፍ ችለዋል፡፡
የሴቶች ማራቶን ውድድር ከ1ኛ እስከ 12ኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተቆጣጥረውታል፡፡
የቫሌንሲያ ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ
በወንዶች ደግሞ አዲሱ ጎበና፣ ለሚ ዱሜቻ እና ደጀኔ መገርሳ ከአንደኛ እስከ ሶተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው በማጠናቀቅ አሸንፈዋል፡፡
ውድድሩን ትግስት ከተማ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ07 ማይክሮ ሰከንድ ስታጠናቅቅ አዲሱ ጎበና ደግሞ 2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ችለዋል፡፡
በወንዶች የማራቶን ውድድርም ከ15ኛ ደረጃ ውጪ ከ1ኛ እስከ 21ኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተቆጣጥረው አጠናቀዋል፡፡