ስፖርት
በማራቶን ታሪክ 2ኛው ፈጣኑ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዘንድሮው የለንደን ማራቶን ይጠበቃል
የለንድን ማራን የ2022 አሸናፊው አሞስ ኪፕሩቶ የአለም ሻምፒዮን ታምራት ቶላ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል
እንግሊዛውዊ አትሌት ሞ ፋራህ በለንደን ማራን የስንብት ውድድሩን እንደሚያደርግ ተነግሯል
በማራቶን ታሪክ እጅግ ፈጣኑ ሁለተኛው ሰው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን ሚያዝያ ወር በሚካሄደው የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ ተነግሯል።
ከዓለማችን አምስቱ ፈጣን ሯጮች መካከል አራቱ እርስ በእርስ የሚፋለሙበትን የለንደን ማራቶን የወንዶች ውድድርን ቀነኒሳ በቀለ ኤሊት የወንዶች ውድድሩን ይመራል።
የሶስት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ ማራቶን 2 ሰአት ከ1 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በማራቶን ታሪክ ሁለተኛው የፈጣን ሰዓት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል ።
የለንደን ማራቶን የ2022 አሸናፊው አሞስ ኪፕሩቶ የአለም ሻምፒዮን ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቀውም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ሞስነት ገረመው ፣ ብርሀኑ ለገሰ እና ልዑል ገብረስላሴ በውድድሩ ኢትዮጵያን ሚወክሉ አትሌቶች ናቸው ተብሏል።
የአራት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ በዚህ ውድድር ላይ የስንብት የሩጫ ውድድሩን እንደሚያደርግም ይጠበቃል ተብሏል።
የለንደን ማራቶን የአራት ጊዜ አሸናፊው እና የማራቶን የክብረወሰን ባለቤት ኤሉድ ኪፕቾጌ ከዝንድሮ የለንደን ማራቶን ውጪ መሆኑ ተሰምቷል።