ከፕሪሚየር ሊጉ በመቀጠል የውጭ ተጨዋቾችን በማሰለፍ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያለው ፈርስት ዲቪዥን ነው
በአውሮፖ ሀገራት የሚገኙ የእግር ኳስ ሊጎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የውጭ ተጨዋቾችን አሰልፈዋል።
የውጭ ተጨዋቾችን ካሰለፉት ሊጎች መካከል የእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ እና የሲፕረሱ ፈርስት ዲቪዥን ቀደሚ መሆናቸውን ስካይ ኒውስ በዘንድሮው አመት ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ካሉት ተጨዋቾች 69.2 በመቶ የውጭ ሀገር ተጨዋቾች ናቸው። ከፕሪሚየር ሊጉ በመቀጠል የውጭ ተጨዋቾችን በማሰለፍ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያለው ፈርስት ዲቪዥን ካሉት ተጨዋቾች ውስጥ 57.1 በመቶ የሚሆኑት የውጭ ተጨዋቾች መሆናቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
የቤልጀሙ ጁፒለር ፕሮ ሊግ እና የፖርቱጋሉ ሊጋኖስ የውጭ ተጨዋቾችን በማስከተል በቅደም ተከተል አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከአውሮፖ ሊጎች ውስጥ ከፍተኛ ብዝሃነት ያለበት ነው። በሊጉ ከ65 በላይ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾች ይገኛሉ።