የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ 1 ዶላር በ103 ብር እገዛ፤ በ114 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 10 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 5 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 10 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ትናንት ሲገዛበት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ በሆነ ዋጋ በ103.9699 ብር እየገዛ ይገኛል። መግዣው ላይም በተመሳሳይ ጭማሪ ሳያደርግ 114.6768 ብር እየገዛ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ127.7381 ብር እየገዛ በ141.5151 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.7514 ብር እየተገዛ በ117.3216 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ወጋገን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.2196 ብር እየተገዛ በ116.2760 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.1561 ብር እየተገዛ በ117.6963 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ዳሽን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ103.9999 ብር እየተገዛ በ116.4798 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን አስታውቋል።