ኢኮኖሚ
የነሃሴ 6 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ምን ይመስላል?
ልማት ባንክና የግል ባንኮች የ1 ዶላርን እስከ 108 ብር እየገዙ እስከ 117 ብር እየሸጡ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ 1 ዶላር በ101 ብር እገዛ፤ በ111 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ ከ50 ብር በላይ ጭማሪ ታይቷል።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 6 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 7 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዛሬው እለት 1 የአሜሪካ ዶላርን በ108 በር እየገዛ በ115 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
በፀሃይ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ103.3312 ብር እየተገዛ በ115.7309 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.2298 ብር እየተገዛ በ116.7374 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከግል ባንኮች ዝቅ ያለ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አውጥቷል። ባንኩ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.8041 ብር እየገዛ በ111.9845 ብር እየሸጠ ነው።