የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ 1 ዶላር 102 ብር እየገዛ፤ በ113 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ አዲስ የምንዛሬ ዋጋ በማውጣት ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 7 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ትናንት ሲገዛበት ከነበረው አንድ ብር ጨምሮ 102.9889 ብር አድርሶታል። መግዣው ላይም ተመሳሳይ ጭማሪ በማድረግ 113.2889 ብር እየገዛ ይገኛል።
የእንግዝሊ ፓውንድ በ125.5507 ብር እየገዛ በ138.7004 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ባወጣው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላርን በ103.9831 ብር እየገዛ በ119.5806 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
አዋሽ ባንክ ባወጣው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላርን በ103.9151 ብር እየገዛ በ116.2082 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.2298 ብር እየተገዛ በ116.7374 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።