ዲያስፖራዎች ለሀገራቸውን የሚያደርጉትን አስዋጽኦ የሚወስኑ ጉዳዮች ምንድናቸው?
ዲያስፖራዎች ለተወለዱበት ሀገር የሚያደርጉት የኢኮኖሚ አበርክቶ የሚወሰኑ በርካታ ገዳዮች መኖራቸው እሙን ነው
ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ዲያስፖራዎች በእውቀት ሽግግር፣ በስራ ፈጠራ እና ሲመሉ ኢንቨስትመንት በማድረግ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ
ዲያስፖራዎች ለሀገራቸውን የሚያደርጉትን አስዋጽኦ የሚወስኑ ጉዳዮች ምንድናቸው?
ዲያስፖራዎች ለተወለዱበት ሀገር የሚያደርጉትን የኢኮኖሚ አበርክቶ የሚወሰኑ በርካታ ገዳዮች መኖራቸው እሙን ነው።
1) የዲያስፖራዎች ብዛት
ከፍተኛ የዲያስፖራ ቁጥር ያላቸው ሀገራት ለሀገራቸው ኢኮኖሚ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍ ይላል
2) የገቢ መጠን
ዲያስፖራዎች የሚያገኙት የገቢ መጠን ከፍ ያለ ከሆነ የሚኖራቸው አስተዋጽኦም በዚያው ልክ ትልቅ ነው።
3) ሪሚታንስ
ወደ ሀገራቸው የሚልኩት ገንዘብ በተለይም በማድግ ላይ ባሉ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
4) የችሎታ ደረጃ
ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ዲያስፖራዎች በእውቀት ሽግግር፣ በስራ ፈጠራ እና ሲመሉ ኢንቨስትመንት በማድረግ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
የትውልድ ሀገር የኢኮኖሚ ሁኔታ፦
ብዙ ጊዜ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ኢኮኖሚያቸው ዲያስፖራዎች በሚልኩት ገንዘብና እና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በሚያደርጉት የልምድ ልውውጥ ላይ የተመሰረተ ነው።
ዲያስፖራዎች በቀጥታ የሚልኩት ገንዘብ ወይም ሪሚታንስ ቤተሰባቸውን የመደገፍ እና የሀገር ኢኮኖሚን የማነቃቃት አቅም ይኖረዋል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ሪሚታንስ ኢንቨስትመንት እንዲጨምር፣ ድህነት እንዲቀንስ እንዲሁም ለጤና እና ለትምህርት ድጎማ ለማድረግ ይጠቅማል።
በውጭ ቆይተው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ሰዎች ኢንቨስትመንት በማድረግ የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ከሚያገኙት ገቢ ግብር በመክፈል እና እውቀት በማስተላለፍ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።