የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የሚጋጥሟቸው ፈተናዎች
የባህር በር የሌላቸው ሀገር በርካታ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል
ባህር አልባ መሆን ከባድ ችግር የሚያስከትል ቢሆንም ጥቂት ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በስትራቴጂክ ወዳጅነት እና በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ችግሮችን ማቃለል ችለዋል
የባህር በር የሌላቸው ሀገር በርካታ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል።
ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።
ውስን የሆነ የባህር በር ተደራሽነት
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጥታ ውቅያኖስ ጋር መድረስ ስለማይችሉ የሸቀጦችን ምልልስ ውድ እና ጊዜ የሚፈጅ በማድረግ በአለምአቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።
ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት ወጭ
ሀገራት የባህር በር የማይኖራቸው ከሆነ ለትራንስፖርት እና ለማሪታይም ንግድ መስመር በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህ ጥገኝነት ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው።
ባህር በር አልባነት ለከፍተኛ የሸቀጦች ማመላለሻ ወጭ ይዳርጋል።
ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች
የባህር በር አልባነት በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እና በአለምአቀፍ ንግድ ለመሳተፍ ይቸገራሉ።
የትራንስፖርት መስተጓጎል
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በፖለቲካዊ ግጭቶች፣ በተፈጥሮ አደጋዎች እና በመሰረተ ልማት ምክንያት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሊስተጓጎል ይችላል።
የፖለቲካ እና የጸጥታ ችግሮች
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ሸቀጦች በሚያስገቡበት ወቅት በጠረፍ ካሉ ሀገራት ጋር አለመግባባት ሊያጋጥማቸው ይችላል።
በጎረቤት ሀገራት ያሉ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ባህር በር በሌላቸው ሀገራት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳደር ይችላል።
የማሪታይም ሀብቶችን የማግኘት ችግር
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ለኢኮኖሚ እድገት መሰረታዊ የሆኑትን እንደ አሳ እና የነዳጅ ክምችትን ማግኘት አይችሉም።
የቱሪዝም አቅምን ያቀጭጫል
የባህር ጠረፍ አለመኖር የጎብኝዎችን ፍላጎት እና ቁጥር ይቀንሳል። ይህ ከቱሪዝም እና ከተያያዥ ጉዳዮች የሚገኘውን ገቢ እንዲቀንስ ማድረጉ አይቀርም።
ባህር አልባ መሆን ከባድ ችግር የሚያስከትል ቢሆንም ጥቂት ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በስትራቴጂክ ወዳጅነት እና በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ችግሮችን ማቃለል ችለዋል።