ዲቫሉየሽን በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል?
ይዲቫሉየሽን በብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ በብዙ መልኩ ተጽዕኖ ያሳድራል
ዲቫሉየሼን የአንድን ሀገር ገንዘብ የመግዛት አቅም በአንጻራዊነት ከሌሎች ሀገራት ዝቅ ማድረግ ነው
ዲቫሉየሽን በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል?
የገንዘብን የመግዛት አቅም ማዳከም ወይም ዲቫሉየሼን የአንድን ሀገር ገንዘብ የመግዛት አቅም በአንጻራዊነት ከሌሎች ሀገራት ዝቅ ማድረግ ነው።
ይህ በብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ በብዙ መልኩ ተጽዕኖ ያሳድራል።
1) ኢምፖርት እና ኤክስፖርት
የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ወደ ውጭ የሚላኩ ሸቀጦች ርካሽ እንዲሆኑ እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ደግሞ ውድ እንዲሆኑ ያደርጋል። ይህ የሀገርን የውጭ ንግድ ውድድር የሚያጠናክር ሲሆን ወደ ውስጥ የሚገቡ ሸቀጦች እጅግ ውድ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።
2) የኑሮ ውድነት /ኢንፍሌሽን
ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ ስለሚጨምር፣ የገንዘብን የመግዛት አቅም ማዳከም ለኑሮ ወድነት ወይም ኢንፍሌሽን አስዋጽኦ ያበረክታል።
3) የውጭ ብድር
አንድ ሀገር ያለባትን የውጭ ብድር የምትከፍለው በውጭ ምንዛሪ ከሆነ የገንዘብን አቅም ማዳከም እዳውን መልሶ ለመክፈል ውድ ያደርገዋል
4) ቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት
የገንዘብን አቅም ማዳከም ቱሪስቶች እና የውጭ ባለሀብቶች የበለጠ ወደ ሀገር እንዲገቡ ያበረታታቸዋል። ገንዘብ ሲዳከም ቱሪዝም እና የውጭ እንቨትመንት ይጨምራል።
በአጠቃላይ የገንዘብን የመግዛት አቅም ማዳከም አንድ ሀገር ባላት የኢምፖርት እና ኤክስፖርት ጥገኝነት፣ የብድር ሁኔታ እና መንግስት እና ብሔራዊ ባንክ በሚተገብሩት ፖሊሲ ይወሰናል።