በሽር አላሳድን ስላስወገደው ታጣቂ ቡድን "ሀያት ታህሪር አል ሻም" ያሉ እውነታዎች
በሀያት ታህሪር አልሻም የሚመሩት የሶሪያ አማጺያን ለ24 አመታት ያህል ሶሪያን ያስተዳደረውን በሸር አላሳድን ከመንበረ ስልጣኑ አስወግደውታል

ኤችቲኤስ ወይም ከሌሎች ተጽዕኗቸው አናሳ ከሆኑ ቡድኖች ጋር ሆኖ ኢድሊብ እና አካባቢዋን ሲያስተዳደር ቆይቷል
በሀያት ታህሪር አልሻም(ኤችቲኤስ) የሚመሩት የሶሪያ አማጺያን ለ24 አመታት ያህል ሶሪያን ያስተዳደረውን በሸር አላሳድን ከመንበረ ስልጣኑ አስወግደውታል።
አማጺያኑ ከሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል በመነሳት ለ 11 ቀናት ያህል በፈጸሙት መብረቃዊ ጥቃት ነበር የሶሪያ ጦር እንዲፈራርስ፣ አላሳድ ሀገር ጥሎ እንዲሰደድ ያደረጉት።
ኤችቲኤስ ወይም (ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነትን ከማቋረጡ በፊት ጃሀት አል ኑስራ ) ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ሳምንት ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ከሌሎች ተጽዕኗቸው አናሳ ከሆኑ ቡድኖች ጋር ሆኖ ኢድሊብ እና አካባቢዋን ሲያስተዳደር ቆይቷል።
በ 2011 በሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ የተፈለፈሉ ታጣቂ ቡድኖች በሶሪያ ጦር ላይ ውጊያ ከፍተው የነበረ ሲሆን በደርዘን የሚቆጠሩት በሶሪያ ጦር እና በሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ተሸንፈዋል።
ነገርግን "አል ኑስራ ግንባር" ወይም በአሁኑ ስሙ "ሀያት ታህሪር አልሻም" ችግሮችን ተቋቁሞ የቆየ እና ከአላሳድ ውድቀት በፊት በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ "በጣም ጠንካራ" የሚባል ታጣቂ ቡድን ነበር።
ኤችቲኤስ እንዴት ተቋቋመ?
ከ2012-2013 (የመጀመሪያ ምዕራፍ)
-ኤችቲኤስ በጃሀት አል ኑስራ በሚለው ስም ይንቀሳቀስ ነበር
-የተቋቋመው እና የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው አይኤስአይኤስ ከተባለው እስላማዊ ታጣቂ ነበር።
2013-2016( ሁለተኛ ምዕራፍ)
-ከአይኤስአይኤስ ተለየ
-ተጠሪነቱ ለአልቃኢዳ መሆኑን አወጀ
2016-2017(ሶስተኛ ምዕራ )
-ከአልቃኢዳ ጋር የነበረውን ግንኙነት ችግር ገጠመው
-በጃሀት ፋቴህ አል ሻም በሚል ስም ከሌሎች ታጣቂዎች ጋር ጥምረት ፈጠረ
2017-2024(አራተኛው ምዕራፍ)
-ከአልቃኢዳ ጋር በይፋ ተለያየ
- ሀያት ታህሪር አልሻም(ኤችቲኤስ) በሚል ስም ከሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ጋር ጥምረት ፈጠረ
ኤችቲኤስ ስር ያሉት አራት ታጣቂ ቡድኖች
-ኑር አልዲን አል ዜንክ እንቅስቃሴ
-ሊዋ አል ሀቅ
-አንሳር አልዲን ግንባር
- ጃይሽ አል ሱና
ኤችቲኤስ ከአልቃኢዳ ጋር ከተለያየ በኋላ አለምአቀፍ ጂሀድ የሚለውን ሀሳብ በመተው ትኩረቱን ሶሪያ ውስጥ ብቻ በማድረግ በሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ላይ ያለውን ተጽዕኖ አጠናከረ። ይህ ቡድን ሶስት ሚሊዮን ህዝብ ያለባትን ኢድሊብ እና አካባቢዋን በመቆጣጠር መንግስት ሆኖ ግብር እያስከፈለ ለበርካታ አመታት መቆይትም ችሏል። ቡድኑ ሌሎች ታጣቂ ቡድኖችን በመምራት ፕሬዝደንት አላሳደን በማስወገድ ጠንካራ መሆኑንም አስመስክሯል።