ከሳሽ የሆነው የፕሬዘዳንቱ ልጅ ካዌቺ መንግስት የፕሬዘዳንቱን አስከሬን ከፍላጎታቸው ውጭ በመሪዎች መቀበሪያ ቦታ የመቅበር እቅድን ተቃውሞ ከሷል
የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትና የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዘዳንት የሆኑት ኬኔት ካውንዳ የቀብር ቦታ የት ይሁን በሚለው ጉዳይ ቤተሰቦቻቸው ከመንግስት ጋር አልተስማሙም፡፡
ከኬኔት ልጆች መካከል አንደኛው በቀብር ቦታው ጉዳይ በፍርድ ቤት ክስ ቢያቅርብም፣የፕሬዛዳንቱ ስርአተ ቀብር በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡ ካውንዳ ዛምቢያ ነጻነቷን ካገኘችበት ከፈረንጆቹ 1964 ጀምሮ በምርጫ ተሸንፈው ስልጣን እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስ ዛምቢያን መርተዋል፡፡
ካውንዳ ታመው ሉሳካ በሚገኘው ወታደራዊ ሆስቲታል ከገቡ በኋላ በፈረንጆቹ ሰኔ 17 ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡ ካዌቺ የተባለው የፕሬዛዳንቱ ልጅ መንግስት የአባቱን አስከሬን የቀድሞ ፕሬዘዳንቶች በተቀበሩበት ቦታ መቅበር ከፕሬዘዳንቱ ፍላጎት ውጭ ነው በማለት በፍርድ ቤት እየተከራከረ ነው፡፡
ካዌቺ መንግስት የፕሬዘዳንቱን አስከሬን ከፍላጎታቸው ውጭ በኢምባሲ ፓርክ ለመቅበርና፤አስከሬኑን ቆፍሮ በማውጣት ፕሬዘዳንቱ ወደሚፈልገው ቦታ መቅበር እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡ ካዌች እንዳለው ፕሬዘዳንቱ በመኖሪያ ቦታቸው ከ10 አመት በፊት ከሞቱት ሚስታቸው ከቤቲ ጎን መቀበር ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡
የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አብራሃም ምዋንሳ በፕሬዘዳንታዊ የቀብር ቦታ ለመቅበር የታሰበውን እቅድ የሚቃረን የፍርድቤት ትእዛዝ አልደረሰንም ብለዋል፡፡ ምዋንሳ በህግ የሚገዙ መሆናቸውንና የፍርድ ቤት ትእዛዝ ቢኖር እንደሚቀበሉ ተናግረዋል፡፡
ካዌቸ ጠበቃ እንደተናገሩት ከሆነ ሮብ እለት አጋማሽ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያሳልፋል ያሉ ሲሆን ነገርግን ፍርድቤቱ የመንግስት የቀብር ስነስርአት እቅድ የሚያግድ ትእዛዝ አላወጣም፡፡ የአፍሪካ መሪዎችና ዲፕሎማቶች በኒሞኒያ ምክንያት በ97 አመታቸው ለሞቱት የነጻነት አባት ሀዘናቸውን ገልጸዋል፡፡
ኬኔት ካውንዳ ከኢትዮጵያ አጼ ሀይለስላሴ፤ከጋናው ክዋሜ ንኩሩማህ ከኬንያው ጆሞ ኬንያታ ፤ከታንዛኒያው ጁሊየስ ኒሬሬ እና ሌሎችም ጋር በመሆን የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በፈረንጅቹ 1963 ዓመት መመስረታቸው ይታወሳል።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከስምንት ዓመት በፊት በ2013 ዓመት ስሙን ወደ አፍሪካ ህብረት ሲቀይር ድርጅቱን ከመሰረቱ መሪዎች መካከል በህይወት የተገኙት ኬኔት ካውንዳ ብቻ ነበሩ።