የድርጅቱ መስራችና የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ኬኔት ካውንዳ ታመው ሆስፒታል ገብተዋል
አሁን የአፍሪካ ህብረት ከመባሉ በፊት የነበረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት የዛምቢያ የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ኬኔት ካውንዳ ታመው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል።
የዛምቢያ ፕሬዘዳንታዊ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ኬኔት ካውንዳ በሀገሪቱ መዲና ሉሳካ በሚገኝ ሜና ሶካ በተሰኘ የህክምና ማዕከል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አክሎም ሁሉም ዛምቢያዊያን ለነጻ አውጪያቸው እንዲጸልዩላቸው ጠይቋል።
የአሁኑ የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ኤድጋር ሊንጉ በትዊተር ገጻቸው ፈጣሪ ኬኔት ካውንዳን እንዲምራቸው ጸልዩ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ኬኔት ካውንዳ ከኢትዮጵያ አጼ ሀይለስላሴ፤ከጋናው ክዋሜ ንኩሩማህ ከኬንያው ጆሞ ኬንያታ ፤ከታንዛኒያው ጁሊየስ ኒሬሬ እና ሌሎችም ጋር በመሆን የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በፈረንጅቹ 1963 ዓመት መመስረታቸው ይታወሳል።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከስመንት ዓመት በፊት በ2013 ዓመት ስሙን ወደ አፍሪካ ህብረት ሲቀይር ድርጅቱን ከመሰረቱ መሪዎች መካከል በህይወት የተገኙት ኬኔት ካውንዳ ብቻ ነበሩ።