ፖለቲካ
ታመው የነበሩት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች ኬኔት ካውንዳ አረፉ
ድርጅቱ ወደ አፍሪካ ህብረት ስሙን ሲቀይር በህይወት የተገኙት መስራች መሪ ኬኔት ካውንዳ ብቻ ነበሩ
ኬኔት ካውንዳናኢትዮጵያው አጼ ኃይለሳላሴ ከድርጅቱ መስራች መሪዎች መካከል ነበሩ
ለህክምና ሆስፒታል ገብተው የነበሩት የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራችና የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዘዳንት የነበሩት ኬኔት ካዉንዳ ህይወታቸው ማለፉን ኒው ዚምባብዌ የተሰኘው የሀገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ህይወታቸው ያለፈው በሳምባ ምች ምክንያት መሆኑን ጋዜጣው ጨምሮ ጠቅሷል፡፡
የአሁኑ አፍሪካ ህብረትን ወይም የቀድሞውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች ከመሰረቱት መካከል አንዱ የሆኑት የዛምቢያ የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ኬኔት ካውንዳ ታመው ሆስፒታል ገብተው ነበር፡፡
ባለፈው ሳምንት የአሁኑ የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ኤድጋር ሊንጉ በትዊተር ገጻቸው ፈጣሪ ኬኔት ካውንዳን እንዲምራቸው ጸልዩ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈው ነበር፡፡
ኬኔት ካውንዳ ከኢትዮጵያ አጼ ሀይለስላሴ፤ከጋናው ክዋሜ ንኩሩማህ ከኬንያው ጆሞ ኬንያታ ፤ከታንዛኒያው ጁሊየስ ኒሬሬ እና ሌሎችም ጋር በመሆን የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በፈረንጅቹ 1963 ዓመት መመስረታቸው ይታወሳል።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከስምንት ዓመት በፊት በ2013 ዓመት ስሙን ወደ አፍሪካ ህብረት ሲቀይር ድርጅቱን ከመሰረቱ መሪዎች መካከል በህይወት የተገኙት ኬኔት ካውንዳ ብቻ ነበሩ።