ሩሲያ የፊንላንድ አባል መሆን “የመከላከያ እርምጃዎችን” እንድትወስድ እንደሚያስገድዳት ገልጻለች
ፊንላንድ የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት የሆነውን ኔቶን በትናንትናው እለት በይፋ ተቀላቅላለች፤ ባንዲራዋም ብራሰልስ በሚገኘው የጥምረቱ ዋና መስሪያ ቤት ግቢ ተውለብልቧል።
- የቱርክ ፓርላማ የፊንላንድን የኔቶ አባልነት አፀደቀ፤ ስዊድን እየጠበቀች ነው
- ቱርክ፤ ስዊድን እና ፊንላንድ የአንካራን የጸጥታ ችግር ለመፍታት እርምጃ መውሰዳቸውን ገለጸች
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደው ልዩ ያለችው ወታደራዊ ዘመቻ የፖሊሲ ለውጥ እንዲኖር እና ከሩሲያ ጥቃት ሊመጣ ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል።
የፊንላንድ መቀላቀል ኔቶ ከሩሲያ ጋር የሚጋራውን የድንበር ርዝመት በግምት በእጥፍ ያሳድገዋል እና የዩክሬን ጦርነት በእይታ ውስጥ እያለ በመምጣቱ ምስራቃዊ ግንባሩን ያጠናክራል።
የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ በኔቶ ዋና መስሪያ ቤት ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ይፋዊ ሰነድ በማስረከብ የመቀላቀል ሂደቱን አጠናቀዋል።
የፊንላንድ ባንዲራ - በነጭ ጀርባ ላይ ያለ ሰማያዊ መስቀል - ከህብረቱ 30 አባላት ጎን ለጎን ዘወታደራዊ ባንድ ታጅቦ በይፋ ተሰቅሏል።
"ለ75 አመታት ያህል ይህ ታላቅ ህብረት ሀገሮቻችንን ከለላ አድርጎ ዛሬም እንደቀጠለ ነው" ብሏል ኔቶ።
ስቶልተንበርግ ቀደም ሲል የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኔቶ የምስራቅ ክፍል መስፋፋትን ዘመቃወም ዩክሬንን ለመውረር እንደ አንድ ምክንያት መጥቀሳቸው ይታወሳል።
ስቶልተንበርግ በብራስልስ “እሱ በትክክል ተቃራኒውን እያገኘ ነው… ዛሬ ፊንላንድ እና በቅርቡ ስዊድንም ሙሉ የኅብረቱ አባል ትሆናለች" ብለዋል።
የፊንላንድ ፕሬዝዳንት ሳውል ኒኒስቶ ፊንላንድ ለኔቶ የጋራ መከላከያ የምታበረክተው ከፍተኛ አስተዋፅዖ የራሷን ግዛት መከላከል ነው ብለዋል። ይህንን ከኔቶ ጋር ለማስተባበር አሁንም ትልቅ ስራ ይቀራል ብለዋል ።
ኒኒስቶ ከስቶልተንበርግ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "ይህ ለፊንላንድ ታላቅ ቀን ነው እና ለኔቶ አስፈላጊ ቀን ነው ማለት እፈልጋለሁ" ብለዋል።
ክሬምሊን ሩሲያ የፊንላንድ አባል መሆን “የመከላከያ እርምጃዎችን” እንድትወስድ ያደርጋታል ብሏል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ሾይጉ እንደገለጹት እርምጃው በዩክሬን ያለው ግጭት የበለጠ ሊባባስ የሚችልበትን እድል ከፍ አድርጎታል።
ፊንላንድ ኔቶን ለተቀላቀለችበት ምላሽ ሩሲያ በምእራብ እና በሰሜን ምዕራብ ክልሎች ወታደራዊ አቅሟን እንደምታጠናክር ትናገራለች።
የዩክሬን መንግስት የፊንላንድን እርምጃም አድንቋል። የፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ዋና ሰራተኛ የሆኑት አንድሪይ ይርማክ በቴሌግራም ላይ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፤ "ፊንላንድ ትክክለኛውን ምርጫ አድርጋለች፤ ኔቶ ለዩክሬን ቁልፍ ግብ ነው።"