ፊንላንድ በአውሮፓ ዝቅተኛ የወሊድ መጠን ያስመዘገበች ሀገር ሆነች
የፊንላንድ የ2022 የወሊድ መጠን 44ሺህ 933 ሲሆን በ2021 ከነበረው በ 9 ነጥብ 4 በመቶ ያነሰ ነው ተብሏል
ፊንላንድ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከፍተኛውን የሞት መጠን ያስመዘገበች ሀገር መሆኗም ተገልጿል
ፊንላንድ በአውሮፓ በ150 ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛ የወሊድ መጠን ያስመዘገበች ሀገር ሆነች።
በፊንላንድ የስታትስቲክስ ዋና ዳይሬክተር ጁናስ ቶይቮላ የተመዘገበው ያልተጠበቀ የወሊድ መጠን ማሽቆልቆል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የተፈጠረውን አዲስ አዎንታዊ አዝማሚያ ወደ ኋላ የሚመልስ ነው ብለዋል።
የፊንላንድ ስታቲስቲክስ አሀዛዊ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በ ፈረንጆቹ 2022 የተመዘገበው የወሊድ መጠን 44ሺህ 933 ሲሆን ይህም በ2021 ከነበረው በ 9 ነጥብ 4 በመቶ ያነሰ ነው።
የስታቲስቲክስ ጽ / ቤቱ መውለድን በምታበረታታ ሀገር ላይ የወሊድ መጠኑ በዚህ ደረጃ እንዴት ከፍ ዝቅ ሊል ቻለ ለሚለው ግን በግልጽ ያስቀመጠው ምክንያት የለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፊንላንድ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከፍተኛውን የሞት መጠን ያስመዘገበች ሀገር መሆኗም ብሉምበርግ ዘግቧል ።
በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር ወደ 62 ሺህ 886 ከፍ ብሏል ፣ ይህም ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው በ5 ሺህ 227 እንደጨመረ የሚያመላክት ነው ተብሏል።