በቡሩንዲ እስርቤት በተከሰተ የእሳት አደጋ 38 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ
በአደጋው ሌሎች 69 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል
እስርቤቱ በቡሩንዲ በትልቅነቱ 3ኛ ደረጃ ሲሆን ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት የፖለቲካ እስረኞች የሚገኙበት ነው ተብሏል
የቡሩንዲ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮስፐር ባዞምባንዛ እንደተናገሩት በሀገሪቱ ዋና ከተማ በሚገኘው የጊተጋ እስርቤት በተፈጠረ ከባድ የእሳት አደጋ 38 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ሌሎች 69 ሰዎች ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
የእሳት አደጋው የፈጠረው በኤሌክትሪክ መስመር መቀጣጠል ምክንያት መሆኑን ሳጂቲኤን ዘግቧል፡፡
አንድ እስረኛን ጠቅሶ ኤኤፍፒ እንደዘገበው “እሳቱ ነበልባል ሲወጣ ስናይ፣ከነነፍሳችን ልንቃጠል ነው ብለን መጮህ ጀመርን፤ነገርግን ፖሊስ ትእዛዝ አልደረሰኝም በማለት ያለንበትን ግቢ በር ለመክፈት ፍቃደኛ አልሆነም::”
እስረኛው እንዴት እንዳመለጥኩ አላውቅም፣ነገርግን ሌሎች እስረኞች በእሳት መቃጠላቸውን ጠቅሷል፡፡
በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በፖሊስ መኪና ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ፣ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ ቦታው ህክምና እንደተደረገላቸው ተገልጿል፡፡ ቀይ መስቀል ተጎጅዎችን ለመርዳት በቦታው ተገኝቷል፤ እሳቱ አሁን በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡
የ100 አመት እድሜ ያለውና በቡሩንዲ 3ኛው ትልቁ እስር ቤት ሲሆን እስርቤቱ የፖለቲካ እስረኞች የሚገኙበትና ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት እርስቤት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የእስር ቤት ባለስልጣናት እንዳሉት እስርቤቱ እስከ በፈረንጆቹ ህዳር መጨረሻ ድረስ 1500 እስርኞችን ይዙ ነበር ተብሏል፡፡ እስርቤቱ ሲሰራ ለ400 እስረኞች እንዲሆን ተደርጎም ነበር ተብሏል፡፡