የቡሩንዲ ፍርድቤት የገዥውን ፓርቲ እጩ ምርጫ ማሸነፍ አጸደቀለት
በቡሩንዲ የእርስበእርስ ጦርነት ከፈነዳበት ከፈረንጆቹ 1993 ጀምሮ ፕሬዘዳንታዊ የምርጫ ውድድር ስታካሂድ የመጀመሪያ ነው
የቡሩንዲ የህገመንግስት ፍርድቤት ምርጫው እንከን የሌለው ነው በማለት የገዥውን ፓርቲ እጩ ምርጫ ማሸነፍን አጽቆታል
የቡሩንዲ የህገመንግስት ፍርድቤት ምርጫው እንከን የሌለው ነው በማለት የገዥውን ፓርቲ እጩ ምርጫ ማሸነፍን አጽቆታል
የቡሩንዲ የህገመንግስት ፍርድቤት የባለፈው ወር ምርጫ እንከን የሌለው ነው በማለት የገዥውን ፓርቲ የፕሬዘዳንታዊ እጩ ማሸነፍን አጽድቆለታል፡፡ ፍርድቤቱ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን የተፎካካሪዎችን ቅሬታ ውድቅ አድርጓል፡፡
ይህ ምርጫ በቡሩንዲ የእርስበእርስ ጦርነት ከፈነዳበት ከፈረንጆቹ 1993 ጀምሮ ፕሬዘዳንታዊ የምርጫ ውድድር ስታካሂድ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው፡፡ የገዥው ፓርቲ እጩ የሆኑትና የቀድሞ የጦር ጄነራል የሆኑት ኢቫርስቴ ንዳይሽሜይ ከተቃዋሚ መሪ ከሆኑት አጋቶን ርዋሳና ሌሎች አምስት እጩዎች ጋር ነበር የተወዳደሩት፡፡
የህገመንግስት ፍርድቤቱ ባለፈው ወር የተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ትክክለኛ ነበር፤ በመሆኑም ኢቫርስቴ ንዳይሽሜይ ተመራጭ ፕሬዘዳንት ናቸው ብሏል፡፡
የአሁኑ ፕሬዘዳንት ፔሬ ኑኩርንዚዛ አዲስ ተመራጭ ኢቫርስቴ ንዳይሽሜይ ስልጣን እስከሚረከቡበት ነሀሴ ድረስ በስልጣን ላይ ይቆያሉ፡፡
የቡሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ንዳይሽሜይ በ69 በመቶ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ገልጾ ነበር፡፡ ኮሚሽኑ ምርጫው እጅግ ሰላማዊ ነው ባለው ምርጫ ተቃዋሚ መሪው ርዋሳ 24 በመቶ ድምጽ ማግኘቱንም አስታውቋል፡፡
ከምርጫው በፊት በሀገሪቱ የፖለቲካ ብጥብጥና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ያነጣጠረ እስር፣ እንግልትና ግድያ ሲፈጽም እንደነበር ሮይተርስ የሀገርውስጥ የመብት ተሟጋቾችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የተቃዋሚ መሪው ርዋሳ በግንቦት መጨረሻ አካባቢ ክስ በማቅረብ የምርጫውን ውጤት ጥያቄ ውስጥ አስገብተውት ነበር፡፡
እንደ ርዋሳ ከሆነ መራጮች በሞቱ ሰዎች መታወቂያ ካርድ ሁሉ ሲመርጡ ነበር የሚል ክስ አቅርበው ነበር፡፡ነገርግን ፍርድቤቱ ምርጫውን ጥያቄ ውስጥ የሚስገባ ትክክለኛ ያልሆነ የምርጫ አሰራር አልተስተዋለም ብሏል፡፡