የታንዛኒያ መንግስት በፍቃደኝነት ለሚመለሱት ስደተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ አደርጋለሁ ብላለች
የታንዛኒያ መንግስት በፍቃደኝነት ለሚመለሱት ስደተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ አደርጋለሁ ብላለች
የታንዛኒያ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በታንዛኒያ ምእራባዊ ክፍል የሚገኙ በትንሹ 7ሺ የሚሆኑ የቡሩንዲ ስደተኞች በፍቃፈኝነት ወደ ቤታቸው ለመመለስ መመዝገባቸውን አስታውቀዋል፡፡
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆርጅ ስምባቻውኔ ይህን የተናገሩት በሰሜናዊ ታንዛኒያ አሩሻ ሲሆን ታንዛኒያ በፍቃደኝነት ለሚመለሱት ስደተኞች የሚያስፈልግ ቁሳቁስ በማቅረብ እየተባበረች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት በፍቃደኝነት ላይ በተመሰረተው የመመለስ መፍሃግብር እስካሁን ከ90ሺ በላይ ቡሩንዲያውያን ስደተኞች መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ታንዛኒያና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተውን የስደተኞች መመለስ ምስራቃዊቷ አፍሪካ ቡሩንዲ ከተረጋጋች በፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ ሲቃኝ ነበር፡፡
በአሁኑ ወቅት ታንዛኒያ 164 ሺ በላይ የቡሩንዲ ስደተኞችን እያስተናገደች ነው፡፡