አምስት በጣም አስፈላጊ የባዮጂኦኬሚካል ዑደቶች
ባዮጂኦኬሚካል ዑደቱ በምድር ላይ ላለው ህይወት አስፈላጊ ነው
ከእነዚህ ውስጥም ካርቦን፣ ናይትሮጅን፣ ውሃ፣ ፎስፈረስ እና ሰልፈር ይገኙበታል
የባዮጂኦኬሚካል ዑደት የሚለው ቃል ሰፊ ነው። ቃሉ የሚያመለክተው የተለያዩ ንጥረ-ነገሮች ወይም ውህዶች ከመሬት በላይና በታች እንዴት እንደሚጓጓዙ ነው።
ዑደቱ በምድር ላይ ላለው ህይወት አስፈላጊ ነው።
ብዙ ዑደቶች በዚህ ቃል ስር የሚወድቁ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥም ካርቦን፣ ናይትሮጅን፣ ውሃ፣ ፎስፈረስ እና ሰልፈር ይገኙበታል።
እያንዳንዱ ዑደት የራሱ መንገድ ያለውና ከእያንዳንዱ ዑደት ጋር የተያያዙ ስነ-ተዋልዷዊ፣ ስነ-ምድራዊ እና ኬሚካላዊ ገጽታዎች ጋር ነው።
1. የውሃ ዑደት
"የሃይድሮሎጂካል ዑደት" ተብሎም ይጠራል። የውሃ ዑደት የሚጀምረው ውሃ በሚተንበት ጊዜ እና ወደ የውሃ ሲቀየር ነው።
2. የካርቦን ዑደት
የካርቦን አተሞች በከባቢ አየር እና በምድር መካከል የሚተላለፉበት በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የባዮጂኦኬሚካል ዑደቶች አንዱ ነው።
በርካታ የካርቦን ማከማቻዎች ያሉ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ በምድር ላይ ያሉ ድንጋዮች እና ደለል፣ ውቅያኖሶች እና የውሃ አካላት እና ከባቢ አየር ይገኙበታል።
3. የናይትሮጅን ዑደት
በውስጡም ናይትሮጅን በመሬት ውስጥና ውጭ በተለያዩ ቅርጾች ይሰራጫል።
ከከባቢ አየር ጀምሮ ወደ አፈር እና ከዚያም ህይወት ወዳለው አካል፣ ከዚያም እንደገና ወደ ከባቢ አየር ይመለሳል።
4. ፎስፈረስ ዑደት
ፎስፎረስ በድንጋይ፣ ውሃ፣ አፈር እና በህይወት ያሉ እና በሞቱ ፍጥረታት ውስጥ ይጓጓዛል።
ነገር ግን ዝናብ እና ሌሎች የአየር ሁኔታዎች ድንጋይ ፎስፌት እንዲለቁ ያደርጋሉ።
5. የሰልፈር ዑደት
በአለቶች የአየር ሁኔታ አማካኝነት ምድረ ህይወት በኩል ይለቀቃል። ለከባቢ አየር ሲጋለጥ ከኦክሲጅን ጋር በመዋሃድ ወደ ሰልፌት ይቀየራል። ይህን ውህድ እጽዋትና ተህዋስያን ወስደው ወደ ሌሎች የህይወት ቅርጾች ይቀየራሉ።