የአየር ንብረት ቀውስ "የገሃነምን በር ከፍቷል"- የተመድ ዋና ጸኃፊ
አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንደገለጹት በተጨባጭ ካለው የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ጋር ሲነጻጸር ችግሩን ለመቀነስ የሚደረጉ ጥረቶች አናሳ ናቸው
በበካይ ጋዞች ልቀት የተባባሰውን አሰከፊ የሆነውን የከባቢ አየር ሙቀት መጨመርን እና የሰደድ እሳት አደጋ ለመቀነስ አሁንም እድሉ መኖሩን ዋና ጸሃፊው "በክላይሜት አምቢሽን ሰሚት" ላይ ተናግረዋል
የሰው ልጅ ታዳሽ ያልሆኑ የኃይል ምንጮችን የመጠቀም ሱስ "የገሃነምን በር ከፍቷል" ሲሉ የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናገሩ።
በበካይ ጋዞች ልቀት የተባባሰውን አሰከፊ የሆነውን የከባቢ አየር ሙቀት መጨመርን እና የሰደድ እሳት አደጋ ለመቀነስ አሁንም እድሉ መኖሩን ዋና ጸሃፊው "በክላይሜት አምቢሽን ሰሚት" ላይ ተናግረዋል።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንደገለጹት በተጨባጭ ካለው የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ጋር ሲነጻጸር ችግሩን ለመቀነስ የሚደረጉ ጥረቶች አናሳ ናቸው።
በበካይ ጋዝ ልቀት ላይ ለውጥ የማይመጣ ከሆነ የአለም የሙቀት መጠን በ2.8 ዲግሪ ሴልሸስ ሊጨምር ይችላል ብለዋል ጉተሬዝ።
አለም አሁንም የከባቢ አየር ሙቀት መጠን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ መገደብ እንደምትችል ገልጸዋል።
የከባቢ አየር ሙቀትን 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ለመገደብ እና የአየር ንብረት ለውጥ ከሚያስከትላቸው አደጋዎች መጠበቅ ከፈለግን የአለም መሪዎች ተጨባጭ መረጃ መውሰድ አለባቸው ይላሉ ጉተሬዝ።
ታዳሽ ያልሆነ ኃይል ከመጠቀም ወደ ታዳሽ ኃይል መጠቀም እየተሸጋገርን ነው ያሉት ጉተሬዝ ከፊታችን ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።