ኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ የዓለማችን ጠቃሚው ጉባኤ እንደሚሆን ተገለጸ
የተመድ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከአንድ ወር በኋላ በዱባይ ይካሄዳል
ጉባኤው የአየር ንብረት ለውጥ እና ምግብ ዋስትና ጉዳዮችን ባንድ ላይ የሚነሳበት እንደሚሆን ተገልጿል
ኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ የዓለማችን ጠቃሚው ጉባኤ እንደሚሆን ተገለጸ።
በየዓመቱ የሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወይም ተመድ የአየር ንብረት ለውጥ መድረክ ዘንድሮም ከአንድ ወር በኃላ ይካሄዳል።
የዘንድሮውን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በዱባይ ታስተናግዳለች።
የሊባኖስ ግብርና ሚንስትር አባስ አል ሀጂ ሀሰን ለዓልዐይን እንዳሉት ይህ ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥ ስራዎች ሁነኛ ማሳያ ይሆናል ብለዋል።
ሚንስትሩ አክለውም በመድረኩ ላይ የዓለም አየር ንብረት ለውጥ እና የምግብ ዋስትና አጀንዳዎች ይሆናሉ ያሉ ሲሆን ሁለቱ ጉዳዮች የማይነጣጠሉ ተመሳሳይ አጀንዳዎች መሆናቸውንም ተናግረዋል።
እንደ ሚንስትሩ ገለጻ አረብ ኢምሬትስ የምታዘጋከው ኮፕ28 ጉባኤ ለመላው አረብ እና ለዓለም ህዝቦች ጠቃሚ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
አረብ ኢምሬት ይህንን ጉባኤ ለማዘጋጀት በሚገባ መዘጋጀታን የተናገሩት ሚንስትሩ የዓለማችን ሀገራት መሪዎች ይሳተፉበታልም ብለዋል።