ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ስርአት መተግበር ከጀመረች ዛሬ 34ኛ ቀኗን ይዛለች
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ተግባራዊ ከተደረገ ዛሬ 34ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፥ ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን የሚገዙበትን እና የሚሸጡበትን እለታዊ ዋጋ ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 25 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ትናንት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላር በ105.4304 ብር እየገዛ በ117.0277 ብር እየሸጠ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ132.5631 ብር እየገዛ በ147.8322 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
አዋሽ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ105.4405 ብር እየተገዛ በ118.0934 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ንብ ባንክ ባወጣው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ከሰሞኑ ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.9086 ብር እየተገዛ በ117.4976 ብር እየተሸጠ ነው።
ኦሮሚያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.7820 ብር እየተገዛ በ118.4037 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን አመላክቷል።