ባንኮች 1 ዶላርን ከ116 ብር ጀምሮ እንደሚሸጡም ባወጡት እለታዊ ተመን ጠቁመዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ስርአት መከተል ከጀመረች 27 ቀናት ተቆጥረዋል።
ባንኮችም በማህራዊ ትስስር ገጻቸው የየእለቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 18 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.6038 ብር እየገዛ በ116.0579 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ባንኩ የእንግሊዝ ፓውንድ በ130.5842 ብር እየገዛ በ145.5639 ብር እየሸጠ እንደሚገኝም ገልጿል።
ዳሸን ባንክም ትናንት ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ሳያደርግ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.2016 ብር እየተገዛ በ117.2268 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.9086 ብር እየተገዛ በ117.4976 ብር እየተሸጠ ነው።
ኦሮሚያ ባንክም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.7820 ብር እየተገዛ በ118.4037 ብር እየተሸጠ ይገኛል። ባንኩ በዩሮ እና የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ እና መሸጫ ዋጋ ላይ ግን ማሻሻያ አድርጓል።